የእስራኤል ቤት ለሰባት ቀን አለቀሰላት። ከመሞቷ በፊት ያላትን ሁሉ ለባሏ ለምናሴ የቅርብ ዘመዶችና ለቅርብ ዘመዶቿ አካፈለች።
ሕዝቡም በኢየሩሳሌም በቤተ መቅደስ ፊት ሦስት ወር ደስታ አደረጉ፤ ዮዲትም ከእነርሱ ጋር ተቀመጠች።