ዮዲት እንዲህ አለች፤ “ለአምላኬ በከበሮ መዝሙርን ጀምሩ፥ ለጌታ በጸናጽን ዘምሩለት፤ አዲስን መዝሙር ተቀኙለት፤ አክብሩት፥ ስሙንም ጥሩ።
ዮዲትም ይህቺን የምስጋና መዝሙር በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ትዘምር ጀመረች፤ ሕዝቡም ሁሉ ይህቺን የምስጋና መዝሙር ከእርስዋ ቀጥለው ዘመሩ።