እህል በምትይዝበት ከረጢቷ ከተተችው፤ እንደተለመደው ለጸሎት እንደሚሄዱ ሁለቱም አብረው ወጡ፤ ሰፈሩን አቋርጠው ሸለቆውን ዞረው ወደ ቤቱሊያ ተራራ ወጡ፤ ወደ በሮቿም ደረሱ፤
እህል በምትይዝበት ከረጢትም ጨመረችው፤ ለጸሎት እንዳስለመዱ ሁለቱ ሁሉ በአንድነት ወጡ፤ ከሰፈሩም አልፈው ወደ ሸለቆው ዞሩ፤ ወደ ቤጤልዋ ዐቀበትም ወጡ፤ ወደ ከተማውም በር ደረሱ።