መጽሐፈ ዮዲት 11:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያህ የሰማይን አምላክ ቀንና ሌሊት የምታገለግል፥ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ናት፤ ስለዚህ ጌታዬ ከአንተ ጋር እቆያለሁ፤ ነገር ግን ባርያህ በየምሽቱ ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ ወደ ሸለቆው ትወርዳለች፤ እርሱም ኃጢአትን በሰሩ ጊዜ ይነግረኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ አገልጋይህ እግዚአብሔርን የምፈራ ነኝና የሰማይ አምላክ እግዚአብሔርንም በመዓልትና በሌሊት አገለግለዋለሁ። አቤቱ፥ አሁንም ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤ ነገር ግን እኔ አገልጋይህ ወደ እግዚአብሔር እለምን ዘንድ ሌሊት ወደ ምድረ በዳ እወጣለሁ፤ መቼም የሠሩትን ኀጢአታቸውን ይነግረኛል። |