የይሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤጽ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ አንተም መልሰህ፥ ‘አገልጋይህ ሒታዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”
መሳፍንት 9:53 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዲት ሴት ከላይ የወፍጮ መጅ በራሱ ላይ ለቀቀችበት፤ ጭንቅላቱንም አፈረሰችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዲት ሴት ከላይ የወፍጮ መጅ በአቢሜሌክ ራስ ላይ ለቀቀችበት፤ ጭንቅላቱንም አፈረሰችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አንዲት ሴት በራሱ ላይ የወፍጮ ድንጋይ ናዳ በመጣል አናቱን ፈጠፈጠችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዲትም ሴት በአቤሜሌክ ራስ ላይ የወፍጮ መጅ ጣለችበት፤ አናቱንም ሰበረችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዲትም ሴት በአቤሜሌክ ራስ ላይ የወፍጮ መጅ ጣለችበት፥ አናቱንም ሰበረችው። |
የይሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤጽ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ አንተም መልሰህ፥ ‘አገልጋይህ ሒታዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”
ነገሩስ እንዲህ አይደለም፤ የኰረብታማው የኤፍሬሙ አገር ሰው፥ የቢክሪ ልጅ ሼባዕ እጁን በንጉሡ በዳዊት ላይ አንሥቶአል፤ እናንተ ይህን ሰው ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ከተማዪቱን ትቼ እሄዳለሁ” አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፥ “የሰውየው ራስ ተቆርጦ በግንቡ ላይ ይወረወርልሃል” አለችው።
ስለዚህ ጌታ በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፤ በእውነት የመንጋው ትንንሾች እንኳ ይጐትቷቸዋል፤ በእውነት የማደሪያቸውም በረት በእነርሱ ላይ ይሣቀቃል።
ስለዚህ ጌታ በባቢሎን ላይ የመከረባትን ምክር፥ በከለዳውያንም ምድር ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፤ በእውነት የመንጋው ትንንሾች እንኳ ይጐትቷቸዋል፤ በእውነት የማደሪያውም በረት በእነርሱ ላይ ይሣቀቃል።
ዲቦራ መልሳ፥ “ይሁን እሺ፤ መሄዱን አብሬህ እሄዳለሁ፤ በዚህ ሁኔታ የምትሄድ ከሆነ ግን ክብሩ ለአንተ አይሆንም፤ ጌታ ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና” አለችው። ስለዚህ ዲቦራ ከባራቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች፤
የእሾኽ ቊጥቋጦውም ዛፎቹን፥ “በእርግጥ ቀብታችሁ በላያችሁ የምታነግሡኝ ከሆነ መጥታችሁ በጥላዬ ሥር ተጠለሉ፤ ይህን ባታደርጉ ግን እሳት ከእሾ ቊጥቋጦው ይነሣ፤ የሊባኖስንም ዝግባዎች ይብላ” አላቸው።
ይህ ካልሆነ ግን እሳት ከአቤሜሌክ ትውጣና እናንተን፥ የሴኬምንና የቤትሚሎን ነዋሪዎች ትብላ፤ እንዲሁም እሳት ከእናንተ፥ ከሴኬምና ከቤትሚሎን ነዋሪዎች ትውጣና አቤሜሌክን ትብላ።”