Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 11:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የይሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤጽ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ አንተም መልሰህ፥ ‘አገልጋይህ ሒታዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የይሩቤሼትን ልጅ አቢሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤስ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቅቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ በማለት ቢጠይቅህ፣ አንተም መልሰህ፣ ‘አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የጌዴዎን ልጅ አቤሜሌክ እንዴት እንደ ሞተ አታስታውሱምን? እርሱን ቴቤጽ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ አንዲት ሴት ከግንብ ላይ የወፍጮ ድንጋይ ናዳ በመጣል ገደለችው፤ ታዲያ እናንተ ወደ ግንብ የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ ንጉሡ ይህን ጥያቄ ቢያቀርብልህ፥ ‘የጦር መኰንንህ ኦርዮም ተገድሎአል’ ብለህ ንገረው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የኔር ልጅ የይ​ሩ​በ​ዓ​ልን ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን ማን ገደ​ለው? አን​ዲት ሴት ከቅ​ጥር ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጥላ​በት የሞተ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቅጥሩ እን​ደ​ዚህ ቀረ​ባ​ችሁ? አን​ተም፦ ባሪ​ያህ ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን ማን ገደለው? ከቅጥር ላይ የወፍጮ መጅ ጥላ በቴቤስ ላይ የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ስለ ምን ወደ ቅጥሩ እንደዚህ ቀርባችሁ? ብሎ ንጉሡ ሲቆጣ ብታይ፥ አንተ፦ ባሪያህ ኬጢያዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 11:21
11 Referencias Cruzadas  

የከተማዪቱም ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ጦርነት ገጠሙ፤ ከዳዊት ሠራዊት ውስጥ ጥቂቶቹ ወደቁ፤ እንዲሁም ሒታዊው ኦርዮንም ሞተ።


ንጉሡ በቁጣ ቱግ ብሎ እንዲህ ይልህ ይሆናል፥ ‘ለመውጋት ስትሉ ይህን ያህል ወደ ከተማዪቱ የተጠጋችሁት ስለ ምንድነው? ከግንቡ ቅጥር በላይ ፍላጻ እንደሚሰዱባችሁ አታውቁም ኖሮአል?


ስለዚህ መልእክተኛው ተነሥቶ ሄደ፤ እዚያ እንደደረሰም ከኢዮአብ የተቀበለውን መልእክት በሙሉ ለዳዊት ነገረው።


አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።


“አበኔር እንደ ተራ ሰው ይሙት? እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ ሰው በክፉ ሰዎች ፊት እንደሚወድቅ አንተም እንደዚሁ ወደቅህ።” ሕዝቡም ሁሉ እንደገና አለቀሱለት።


አቤቱ አሁንስ ማንን እጠብቃለሁ? ተስፋዬ በአንተ ነው።።


እነዚህ ሁሉ፦ አንተ ደግሞ እንደ እኛ ደክመሃልን? እኛንስ መስለሃልን?


ስለዚህም፥ “መሠዊያውን አፍርሶበታልና ራሱ በኣል ይሟገተው” ሲሉ በዚያ ዕለት ጌዴዎንን፥ “ይሩበኣል” ብለው ጠሩት።


ይሩበኣል የተባለው ጌዴዎን፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጠዋት ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያንም ሰፈር እስራኤላውያን ከሰፈሩበት በስተ ሰሜን በኩል፥ በሞሬ ኰረብታ አጠገብ በሸለቆው ውስጥ ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos