በዚህ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ቤተ ጣዖቱን ሞልተውት ነበር፤ የፍልስጥኤማውያን ገዦችም በሙሉ በዚያ ነበሩ፤ ሳምሶን ሲጫወት ለማየት ሦስት ሺህ ያህል ወንዶችና ሴቶች በጣራው ላይ ነበሩ።
መሳፍንት 9:51 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆኖም በከተማይቱ ውስጥ ብርቱ ግንብ ስለ ነበር፥ የከተማይቱ ሕዝብ በሙሉ ወንድ ሴት ሳይባል ወደዚያ ሸሹ፤ ደጁንም በውስጥ ዘግተው ወደ ግንቡ ጣሪያ ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም በከተማዪቱ ውስጥ ብርቱ ግንብ ስለ ነበር፣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ፣ የከተማዪቱ ገዦችም ወደዚያ ሸሹ፤ ደጁንም በውስጥ ዘግተው ወደ ግንቡ ጣራ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከተማይቱ ውስጥ አንድ ትልቅ የከተማ መጠበቂያ ግንብ ስለ ነበረ፥ መሪዎቹ ሳይቀሩ እያንዳንዱ ወንድም ሆነ ሴት ሮጦ ወደ እርሱ ገባ፤ በሩንም ዘግተው ወደ ጣራው ወጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርስዋም ተቀመጠ፤ እጅም አደረጋት። በከተማዪቱም ውስጥ ብርቱ ግንብ ነበረ፤ የከተማዪቱም ሰዎች ሁሉ፥ ወንዱና ሴቱ ሁሉ፥ ወደዚያ ሸሹ፤ ደጁንም በኋላቸው ዘጉ፤ ወደ ግንቡም ሰገነት ላይ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከተማይቱም ውስጥ ብርቱ ግንብ ነበረ፥ የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ፥ ወንዱና ሴቱ ሁሉ፥ ወደዚያ ሸሹ፥ ደጁንም በኋላቸው ዘጉ፥ ወደ ግንቡም ሰገነት ላይ ወጡ። |
በዚህ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ቤተ ጣዖቱን ሞልተውት ነበር፤ የፍልስጥኤማውያን ገዦችም በሙሉ በዚያ ነበሩ፤ ሳምሶን ሲጫወት ለማየት ሦስት ሺህ ያህል ወንዶችና ሴቶች በጣራው ላይ ነበሩ።