መሳፍንት 8:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌዴዎን የከተማይቱን አለቆች ወሰደ፤ በምድረ በዳ እሾኽና አሜኬላ በመቅጣት የሱኮትን ሰዎች ትምህርት ሰጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌዴዎን የከተማዪቱን አለቆች ወሰደ፤ በምድረ በዳ እሾኽና አሜከላ በመቅጣት የሱኮትን ሰዎች ትምህርት ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እሾኽና አሜከላ ከበረሓ ወስዶ የሱኮትን መሪዎች ገረፋቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከተማዪቱንም ሽማግሌዎችና አለቆች ያዘ፥ የምድረ በዳንም እሾህና ኩርንችት ወስዶ የሱኮትን ሰዎች ገረፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከተማይቱንም ሽማግሌዎች ያዘ፥ የምድረ በዳንም እሾህና ኵርንችት ወስዶ የሱኮትን ሰዎች ገረፋቸው። |
ከእነርሱ የተሻለ የተባለው እንደ አሜከላ ነው፥ ቅን የተባለው እንደ ኩርንችት ነው፤ ጠባቂዎችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቷል፤ መሸበራቸውም አሁን ይሆናል።
ከዚያም ጌዴዎን ወደ ሱኮት ሰዎች መጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “ ‘ለደከሙት ሰዎችህ እንጀራ እንሰጥ ዘንድ ዜባሕና ጻልሙና በእጅህ ገብተዋልን’ በማለት ያላገጣችሁብኝ ዜባሕና ጻልሙና እነዚሁላችሁ።”
ጌዴዎንም መልሶ፥ “እንግዲህ ደህና፤ ጌታ ዜባሕንና ጻልሙናን በእጄ አሳልፎ በሚሰጥበት ጊዜ በምድረ በዳ እሾኽና አሜከላ ሥጋችሁን እገርፋለሁ” አላቸው።