መሳፍንት 5:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዱሮ ጀምሮ የታወቀ ያ የቂሶን ወንዝ፥ የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በኃይል እርገጪ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥንታዊው ወንዝ፣ የቂሶን ወንዝ፣ የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው፤ ነፍሴ ሆይ፤ በኀይል ገሥግሺ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቂሶን ጐርፍ ጠራረጋቸው፤ የጥንቱ የቂሶን ወንዝ በጐርፉ ወሰዳቸው፤ ነፍሴ ሆይ! በርቺ! ገሥግሺ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዱሮ ጀምሮ የታወቀ ያ የቂሶን ወንዝ፥ የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በርቺ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዱሮ ጀምሮ የታወቀ ያ የቂሶን ወንዝ፥ የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በኃይል እርገጪ። |
ኤልያስም “የባዓልን ነቢያት ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዘ፤ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሾን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው።