መሳፍንት 5:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዋክብት ከሰማይ ተዋጉ፥ በአካሄዳቸውም ከሲሣራ ጋር ተዋጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰማያት ከዋክብት ተዋጉ፤ በአካሄዳቸውም ሲሣራን ገጠሙት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰማይ ከዋክብት ተዋጉ፤ በሂደታቸው ሲሣራንም ጦርነት ገጠሙት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዋክብት በሰማይ ተዋጉ፤ በሰልፋቸውም ከሲሣራ ጋር ተዋጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዋክብት ከሰማይ ተዋጉ፥ በአካሄዳቸውም ከሲሣራ ጋር ተዋጉ። |
ጌታም በእስራኤል ፊት አስደነገጣቸው፤ በገባዖንም በጽኑ ውግያ ድል አደረጓቸው፥ በቤትሖሮንም ዐቀበት በሆነው መንገድ ላይ አሳደዳቸው፥ እስከ ዓዜቃና እስከ መቄዳ ድረስ መታቸው።
ከእስራኤልም ልጆች ፊት እየሸሹ የቤትሖሮንን ቁልቁለት በመውረድ ላይ ሳሉ፥ ዓዜቃ እስኪደርሱ ድረስ ጌታ ከሰማይ ታላላቅ ድንጋይ አወረደባቸውና ሞቱ፤ የእስራኤል ልጆች በሰይፍ ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት በለጡ።
ጌታም በእስራኤል ልጆች እጅ አሞራውያንን አሳልፎ በሰጠ ቀን ኢያሱ ለጌታ እንዲህ ብሎ ተናገረ፤ የእስራኤልም ልጆች እያዩ እንዲህ አለ፦ “በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፥ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ፤”
ጌታም ሲሣራንና ሠረገሎቹን ሁሉ በባራቅ ፊት በሰይፍ ስለት እጅግ ተሸንፈው ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ አደረገ፤ ሲሣራም ከሠረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ።
ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያሳርግበት ጊዜ፥ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት ቀረቡ። ጌታ ግን በዚያ ዕለት በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ የነጐድጓድ ድምፅ አንጐዳጐደባቸው፤ እነርሱም እጅግ ተሸበሩ፤ በእስራኤላውያን ፊት ድል ተመተውም ሸሹ።