ንጉሡንም ዖዝያንን እየተቃወሙ እንዲህ አሉት፦ “ዖዝያን ሆይ! ዕጣን ማጠን የተቀደሱት የአሮን ልጆች የካህናቱ ሹመት ነው እንጂ ለጌታ እንድታጥን ለአንተ አይገባህም፤ በድለሃልና ከመቅደሱ ውጣ፤ ከአምላክህም ከጌታ ዘንድ ክብር አያስገኝልህም።”
መሳፍንት 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዲቦራ መልሳ፥ “ይሁን እሺ፤ መሄዱን አብሬህ እሄዳለሁ፤ በዚህ ሁኔታ የምትሄድ ከሆነ ግን ክብሩ ለአንተ አይሆንም፤ ጌታ ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና” አለችው። ስለዚህ ዲቦራ ከባራቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዲቦራ መልሳ፣ “ይሁን ዕሺ፤ መሄዱን ዐብሬህ እሄዳለሁ፤ በዚህ ሁኔታ የምትሄድ ከሆነ ግን ክብሩ ለአንተ አይሆንም፤ እግዚአብሔር ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ይሰጣልና” አለችው። ስለዚህ ዲቦራ ከባርቅ ጋራ ወደ ቃዴስ ሄደች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም “እሺ፥ እኔም ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ስለሚሰጥ ድሉ ለአንተ ክብር አይሆንም” አለችው፤ ስለዚህ ዲቦራ ከባራቅ ጋር ወደ ቃዴስ ዘመተች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዲቦራም፥ “በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲሣራን በሴት እጅ አሳልፎ ይሰጣልና በዚህ በምትሄድበት መንገድ ለአንተ ክብር አይሆንም” አለችው። ዲቦራም ተነሥታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሷም፦ በእውነት ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲሣራን በሴት እጅ አሳልፎ ይሰጣልና በዚህ በምትሄድበት መንገድ ለአንተ ክብር አይሆንም አለችው። ዲቦራም ተነሥታ ከባርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች። |
ንጉሡንም ዖዝያንን እየተቃወሙ እንዲህ አሉት፦ “ዖዝያን ሆይ! ዕጣን ማጠን የተቀደሱት የአሮን ልጆች የካህናቱ ሹመት ነው እንጂ ለጌታ እንድታጥን ለአንተ አይገባህም፤ በድለሃልና ከመቅደሱ ውጣ፤ ከአምላክህም ከጌታ ዘንድ ክብር አያስገኝልህም።”
ወዲያውም ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፥ “‘ሴት ገደለችው’ እንዳይሉ እባክህ ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ” አለው። ስለዚህ አገልጋዩ ወጋው፤ እርሱም ሞተ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤’ አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ ከእኔ ይራቅ።