መሳፍንት 21:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም፥ “ከእስራኤል ነገዶች ምጽጳ ላይ በጌታ ጉባኤ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን ነው” ሲሉ ጠየቁ፤ ታዲያ ከያቤሽ ገለዓድ አንድም ሰው ለጉባኤው ወደ ሰፈሩ አለመምጣቱን ተረዱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ “ከእስራኤል ነገዶች ምጽጳ ላይ በእግዚአብሔር ጉባኤ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን ነው” ሲሉ ጠየቁ፤ ታዲያ ከኢያቢስ ገለዓድ አንድም ሰው ለጉባኤው ወደ ሰፈሩ አለመምጣቱን ተረዱ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ እንዲህ አሉ፦ “ከእስራኤል ነገዶች መካከል ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ያልመጣ አለን?” እነሆ ከያቤሽ ገለዓድ ወደ ስብሰባው ማንም አልመጣም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “ከእስራኤል ነገድ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ ያልወጣ ማን ነው?” አሉ። እነሆም፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባኤው ማንም አልወጣም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ ከእስራኤል ነገድ ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ያልወጣ ማን ነው? አሉ። እነሆም፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባኤ ማንም አልወጣም ነበር። |
የጌታ መልአክ፦ ሜሮዝን እርገሙ፥ ጌታን በኃያላን መካከል ለመርዳት፥ ጌታን ለመርዳት አልመጡምና የተቀመጡባትን ሰዎች ፈጽማችሁ እርገሙ አለ።
ጥንድ በሬዎች ወስዶ ቆራረጠ፤ ሥጋቸውንም በመልእክተኞች እጅ ልኮ፥ “ሳኦልንና ሳሙኤልን የማይከተል ሰው በሬው እንደዚህ ይቆራረጣል!” ሲል በመላው እስራኤል አስነገረ። ታላቅ ፍርሀት ከጌታ ዘንድ በሕዝቡ ላይ ወደቀ፤ ሕዝቡም እንደ አንድ ሰው ሆኖ ወጣ።
ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፥ “ለያቢሽ ገለዓድ ሰዎች፥ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለያቢሽ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ እጅግ ተደሰቱ።