Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 21:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እነርሱ እንዲህ አሉ፦ “ከእስራኤል ነገዶች መካከል ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ያልመጣ አለን?” እነሆ ከያቤሽ ገለዓድ ወደ ስብሰባው ማንም አልመጣም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም፣ “ከእስራኤል ነገዶች ምጽጳ ላይ በእግዚአብሔር ጉባኤ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን ነው” ሲሉ ጠየቁ፤ ታዲያ ከኢያቢስ ገለዓድ አንድም ሰው ለጉባኤው ወደ ሰፈሩ አለመምጣቱን ተረዱ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከዚያም፥ “ከእስራኤል ነገዶች ምጽጳ ላይ በጌታ ጉባኤ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን ነው” ሲሉ ጠየቁ፤ ታዲያ ከያቤሽ ገለዓድ አንድም ሰው ለጉባኤው ወደ ሰፈሩ አለመምጣቱን ተረዱ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እነ​ር​ሱም፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መሴፋ ያል​ወጣ ማን ነው?” አሉ። እነ​ሆም፥ ከኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባ​ኤው ማንም አል​ወ​ጣም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እነርሱም፦ ከእስራኤል ነገድ ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ያልወጣ ማን ነው? አሉ። እነሆም፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባኤ ማንም አልወጣም ነበር።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 21:8
9 Referencias Cruzadas  

በገለዓድ የሚገኘው የያቤሽ ሕዝብ፥ ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ የፈጸሙትን ግፍ በሰሙ ጊዜ፥


ከሴቶች ልጆቻችን ማንኛይቱንም ለእነርሱ እንዳንድር በመሐላ ቃል ስለ ገባን ከሞት የተረፉት ብንያማውያን ሚስት ያገኙ ዘንድ ምን እናድርግ?” አሉ።


ሠራዊቱን ለመቊጠር በያንዳንዱ ስም በሚጠራበት ጊዜ ከያቤሽ ወገን አንድም ሰው አልነበረም፤


የእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለ፤ “ሜሮዝን ርገሙ! እዚያ የሚኖሩትን ሁሉ ፈጽማችሁ ርገሙ! እነርሱ በእግዚአብሔር ጐን አልቆሙም፤ ስለ እርሱም ለመዋጋት አልተሰለፉም።”


ጥንዱንም በሬዎች ወስዶ ቈራረጣቸው፤ የሥጋውንም ቊራጭ ሁሉ አስይዞ “ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ ወደ ጦርነት የማይወጣ ሰው ቢኖር በሬዎቹ እንደዚህ ይቈራረጡበታል!” ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር መልእክተኞችን ወደ መላው የእስራኤል ምድር ላከ። በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈራ፤ አንድም ሰው ሳይቀር ሁሉም በአንድነት ወጡ።


ከያቤሽ የመጡትንም መልእክተኞች “ነገ ከቀትር በፊት የምናድናቸው መሆኑን ለሕዝባችሁ ንገሩ” አሉአቸው። መልእክቱንም ለያቤሽ ሰዎች በነገሩ ጊዜ የያቤሽ ሰዎች እጅግ ተደሰቱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos