መሳፍንት 21:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዐሥራ ሁለት ሺህ ተዋጊዎች ወደ ያቤሽ ገለዓድ ሄደው በእዚያ የሚኖሩትን በሙሉ ሴቶቹንና ሕፃናቱን ጭምር በሰይፍ እንዲፈጇቸው ጉባኤው መመሪያ ሰጥቶ ላካቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ተዋጊዎች ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ሄደው በዚያ የሚኖሩትን በሙሉ ሴቶቹንና ሕፃናቱን ጭምር በሰይፍ እንዲፈጇቸው ጉባኤው መመሪያ ሰጥቶ ላካቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ጉባኤው “ወደ ያቤሽ ሄዳችሁ ሴቶችና ሕፃናት ሳይቀሩ የገለዓድ ኗሪዎችን በሰይፍ ስለት ግደሉ!” ብለው ዐሥራ ሁለት ሺህ ኀያላንን ላኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኅበሩም ወደዚያ ዐሥራ ሁለት ሺህ ኀያላን ሰዎችን ልከው፥ “ሂዱ በኢያቢስ ገለዓድም ያሉትን ሰዎች ሴቶችንም ሕዝቡንም በሰይፍ ስለት ግደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኅበሩም ወደዚያ አሥራ ሁለት ሺህ ኃያላን ሰዎች ሰድደው፦ ሂዱ በኢያቢስ ገለዓድም ያሉትን ሰዎች ከሴቶችና ከሕፃናት ጋር በሰይፍ ስለት ግደሉ። |
ኢያሱና እስራኤል ሁሉ የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ካባውንም፥ ወርቁንም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያዎቹንም፥ በጎቹንም፥ ድንኳኑንም፥ ያለውንም ሁሉ ወስደው ወደ አኮር ሸለቆ አመጡአቸው።
በምጽጳ፥ በጌታ ጉባኤ ፊት ያልተገኘ ማንኛውም ሰው መገደል አለበት ብለው እስራኤላውያን ተማምለው ስለ ነበር፥ “ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በጌታ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን አለ?” ሲሉ ጠየቁ።
ከዚያም፥ “ከእስራኤል ነገዶች ምጽጳ ላይ በጌታ ጉባኤ ፊት ሳይወጣ የቀረ ማን ነው” ሲሉ ጠየቁ፤ ታዲያ ከያቤሽ ገለዓድ አንድም ሰው ለጉባኤው ወደ ሰፈሩ አለመምጣቱን ተረዱ፤
የጌታ መልአክ፦ ሜሮዝን እርገሙ፥ ጌታን በኃያላን መካከል ለመርዳት፥ ጌታን ለመርዳት አልመጡምና የተቀመጡባትን ሰዎች ፈጽማችሁ እርገሙ አለ።
ጥንድ በሬዎች ወስዶ ቆራረጠ፤ ሥጋቸውንም በመልእክተኞች እጅ ልኮ፥ “ሳኦልንና ሳሙኤልን የማይከተል ሰው በሬው እንደዚህ ይቆራረጣል!” ሲል በመላው እስራኤል አስነገረ። ታላቅ ፍርሀት ከጌታ ዘንድ በሕዝቡ ላይ ወደቀ፤ ሕዝቡም እንደ አንድ ሰው ሆኖ ወጣ።
አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንም ሴቱንም፥ ልጁንም ሕፃኑንም፥ የቀንድ ከብቱንም በጉንም፥ ግመሉንም አህያውንም ግደል።’ ”