መሳፍንት 20:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብንያማውያንንም ከበቧቸው፤ አሳደዷቸው፤ ከጊብዓ በስተ ምሥራቅ ትይዩ ባለውም ስፍራ አሳደው አሸነፏቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብንያማውያንንም ከበቧቸው፤ አሳደዷቸው፤ ከጊብዓ በስተምሥራቅ ትይዩ ባለውም ስፍራ በቀላሉ አሸነፏቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ብንያማውያንን ከበው በጊብዓ በስተ ምሥራቅ እስከሚገኘው ስፍራ ድረስ አሳደው ፈጁአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብንያማውያንንም ወግተው አጠፉአቸው፤ በምሥራቅ በኩል ባለው በገባዖንም ፈጽመው ደመሰሱአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብንያማውያንንም ከበቡ፥ በምሥራቅም በኩል እስካለው እስከ ጊብዓ አንጻር ድረስ አሳደዱአቸው፥ በመኑሔም አጠፉአቸው። |