መሳፍንት 20:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ሰዎች የሸመቀው ጦር በከተማይቱ ውስጥ ከባድ የጢስ ደመና ምልክት እንዲያሳዩ ተስማሙ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ሰዎች ያሸመቀው ጦር በከተማዪቱ ውስጥ ከባድ የጢስ ደመና ምልክት እንዲያሳይ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሸምቀው የነበሩት ሰዎች በከተማው ብዙ የጢስ ደመና እንዲያስነሡ በዋናው የእስራኤል ሠራዊትና ሸምቀው በነበሩት ሰዎች መካከል የምልክት ስምምነት ተደርጎ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተደበቁትም ሰዎች ከከተማው ብዙ ጢስ እንደ ደመና እንዲያስነሡ በእስራኤል ልጆችና በተደበቁት ሰዎች መካከል ምልክት ተደርጎ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተደበቁትም ሰዎች ከከተማው ብዙ ጢስ እንደ ደመና እንዲያስነሡ በእስራኤል ልጆችና በተደበቁት ሰዎች መካከል ምልክት ተደርጎ ነበር። |
ኤልሳዕም “በመጪው ዓመት ልክ ይህን ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት። እርሷም፦ “አይደለም! ጌታዬ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እባክህ የማይፈጸም የተስፋ ቃል አትንገረኝ!” አለችው።
በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የኋላ ደጀን የሆነውን ሕዝብ አኖሩ፤ ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው ውስጥ አደረ።
የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው የከተማይቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሸው ሕዝብ በሚያሳድዱአቸው ላይ ስለ ተመለሱ ወዲህና ወዲያም መሸሽ አልቻሉም።