መሳፍንት 20:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ሰዎች ብንያማውያንን ለመውጋት ሄዱ፤ በጊብዓ ለሚያደርጉትም ውጊያ ቦታ ቦታቸውን ያዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ሰዎች ብንያማውያንን ለመውጋት ሄዱ፤ በጊብዓ ለሚያደርጉትም ውጊያ ቦታ ቦታቸውን ያዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በብንያም ሠራዊት ላይ አደጋ ለመጣል ሄዱ፤ ወታደሮቻቸውንም በጊብዓ ትይዩ አሰለፉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከብንያም ጋር ሊዋጉ ወጡ፤ በገባዖንም ገጠሙአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሰዎች ከብንያም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ የእስራኤልም ሰዎች በጊብዓ አጠገብ በእነርሱ ላይ ተሰልፈው ቆሙ። |