መሳፍንት 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያንን ስፍራ ቦኪምሠ ብለው ጠሩት፤ በዚያም ለጌታ መሥዋዕት አቀረቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያን ስፍራ ቦኪም ብለው ጠሩት፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ ስፍራ “ቦኪም” ተብሎ የተጠራውም በዚህ ምክንያት ነው፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚያም ስፍራ ስም “መካነ ብካይ” ተብሎ ተጠራ፤ በዚያም ለእግዚአብሔር ሠዉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያንም ስፍራ ስም ቦኪም ብለው ጠሩት፥ በዚያም ለእግዚአብሔር ሠዉ። |
በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩ፤ ጌታም ከጽኑ ቁጣው ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ተጠራ።
የጌታ መልአክ ከጌልገላ ወደ ቦኪም ወጥቶ እንዲህ አለ፤ “ከግብጽ ምድር አወጣኋችሁ፤ ለቀደሙትም አባቶቻችሁ ልሰጣቸው ወደ ማልሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፤ እንዲህም አልሁ፤ ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አላፈርስም፤
ጌዴዎንም በዚያ ለጌታ መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም “ጌታ ሰላም ነው” ብሎ ጠራው፤ ይህ መሠዊያ የአቢዔዝራውያን ይዞታ በሆነው በዖፍራ ዛሬም ቆሞ ይታያል።
ስለዚህ ሳሙኤል አንድ የሚጠባ የበግ ግልገል ወስዶ ሙሉ ለሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ለጌታ አቀረበው፤ ስለ እስራኤልም ወደ ጌታ ጸለየ፤ ጌታም መለሰለት።