ቁራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ፥ ስለዚህ ወደ ባርያችሁ መጥታችኋልና።” እነርሱም፦ “እንዳልህ አድርግ” አሉት።
መሳፍንት 19:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአራተኛው ቀን ማልደው ተነሡ፤ እንግዳውም ለመሄድ ተዘጋጀ፤ የልጂቱ አባት ግን፥ “እንድትበረታ እህል ቅመስ፤ ከዚያም መሄድ ትችላለህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራተኛው ቀን ማልደው ተነሡ፤ እንግዳውም ለመሄድ ተዘጋጀ፤ የልጅቱ አባት ግን፣ “እንድትበረታ እህል ቅመስ፤ ከዚያም መሄድ ትችላለህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራተኛው ቀን ጧት በማለዳ ተነሡና ለመሄድ ተዘጋጁ፤ የልጅቱ አባት ግን የልጁን ባል “ብርታት እንድታገኝ መጀመሪያ እህል ቅመስ፤ ከዚያም በኋላ ትሄዳለህ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራተኛውም ቀን ማልደው ተነሡ፤ እርሱም ለመሄድ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱም አባት አማቹን፥ “ሰውነትህን በቁራሽ እንጀራ አበርታ፤ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራተኛውም ቀን ማልደው ተነሡ፥ እርሱም ለመሄድ ተነሣ፥ የብላቴናይቱም አባት አማቹን፦ ሰውነትህን በቁራሽ እንጀራ አበርታ፥ ከዚያም በኋላ ትሄዳለህ አለው። |
ቁራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ፥ ስለዚህ ወደ ባርያችሁ መጥታችኋልና።” እነርሱም፦ “እንዳልህ አድርግ” አሉት።
በአምስተኛውም ቀን ጠዋት ሌዋዊው ለመሄድ ሲነሣ፥ የልጂቱ አባት “ሰውነትህን አበርታ፤ ጥላው እስኪበርድም ድረስ በዚሁ ቈይ” አለው፤ ስለዚህ ሁለቱም አብረው በሉ።
እንደዚሁም የበለስ ጥፍጥፍ ቁራሽና ሁለት ደረቅ የወይን ዘለላዎች ሰጡት። ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም እህል ስላልበላ፥ ውሃም ስላልጠጣ ይህን ከበላ በኋላ ነፍሱ ተመለሰች።