መሳፍንት 19:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤቱ እንደደረሰም ቢላዋ አንሥቶ ቁባቱን ዐሥራ ሁለት ቦታ በመቈራረጥ ወደ እስራኤል ምድር ሁሉ ሰደደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤቱ እንደ ደረሰም ቢላዋ አንሥቶ ቁባቱን ዐሥራ ሁለት ቦታ በመቈራረጥ ወደ እስራኤል ምድር ሁሉ ሰደደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም በደረሰ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ፤ ቢላዋም አንሥቶ የቊባቱን ሬሳ ዐሥራ ሁለት ቦታ ቈራረጠው፤ ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች አንዳንድ ቊራጭ ላከ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ካራ አነሣ፤ ዕቅብቱንም ይዞ ከአጥንቶችዋ መለያያ ላይ ለዐሥራ ሁለት ቈራርጦ ወደ እስራኤል ሀገር ሁሉ ሰደደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ቤቱም በመጣ ጊዜ ካራ አነሣ፥ ቁባቱንም ይዞ ከአጥንቶችዋ መለያያ ላይ ለአሥራ ሁለት ቈራርጦ ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ሰደደ። |
ጥንድ በሬዎች ወስዶ ቆራረጠ፤ ሥጋቸውንም በመልእክተኞች እጅ ልኮ፥ “ሳኦልንና ሳሙኤልን የማይከተል ሰው በሬው እንደዚህ ይቆራረጣል!” ሲል በመላው እስራኤል አስነገረ። ታላቅ ፍርሀት ከጌታ ዘንድ በሕዝቡ ላይ ወደቀ፤ ሕዝቡም እንደ አንድ ሰው ሆኖ ወጣ።