አባቱም በሕይወቱ ሳለ፦ “እንዲህ ለምን ታደርጋለህ?” ብሎ ከቶ ተቆጥቶት አያውቅም ነበር። ደግሞም መልከ መልካም ነበር፤ የተወለደውም ከአቤሴሎም በኋላ ነበር።
መሳፍንት 18:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ አምስቱ ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ላይሽ መጡ፤ ሲዶናውያን ያለ ስጋት በጸጥታ እንደሚኖሩ ሁሉ፥ በዚያም የሚኖረው ሕዝብ በሰላም እንደሚኖር አዩ። ምድሪቱ አንዳች የሚጐድላት ነገር ባለ መኖሩ ሕዝቡ ባለጸጋ ነበር። እንዲሁም ከሲዶናውያን ርቆ የሚኖር ሲሆን፥ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ግንኙነት አልነበረውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዐምስቱ ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ላይሽ መጡ፤ ሲዶናውያን ያለ ሥጋት በጸጥታ እንደሚኖሩ ሁሉ፣ በዚያም የሚኖረው ሕዝብ በሰላም እንደሚኖር አዩ። ምድሪቱ አንዳች የሚጐድላት ነገር ባለመኖሩ ሕዝቡ ባለጠጋ ነበር። እንዲሁም ከሲዶናውያን ርቆ የሚኖር ሲሆን፣ ከማንኛውም ሕዝብ ጋራ ግንኙነት አልነበረውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አምስቱ ሰዎች ከዚያ ሄደው ወደ ላዪሽ ደረሱ፤ በዚያም የነበሩት ኗሪዎች ልክ እንደ ሲዶናውያን በሰላም የሚኖሩ መሆናቸውን ተመለከቱ፤ ሕዝቡም ከማንም ጋር ሳይጋጩ ጸጥ ባለ መንፈስ የሚኖሩ ሰላም ወዳዶች ነበሩ፤ ከዚህም ጋር ከሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ምንም የሚጐድላቸው አልነበረም፤ ከዚህም የተነሣ ከማንኛውም ሕዝብ ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው ከሲዶናውያን በመራቅ ተገልለው ይኖሩ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምስቱም ሰዎች ሄዱ፤ ወደ ሌሳም ደረሱ፤ በውስጡም የነበሩትን ሕዝብ ተዘልለው አዩአቸው፤ እንደ ሲዶናውያንም ልማድ ጸጥ ብለው፥ ዐርፈው፥ ተዘልለውም ተቀምጠው ነበር፤ በተመዘገበች የርስታቸው ምድርም ቃልን መናገር አልቻሉም፤ ከሲዶናውያንም ርቀው ይኖሩ ነበር። ከሶርያውያንም ጋር ግንኙነት አልነበራቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምስቱም ሰዎች ሄዱ ወደ ሌሳም መጡ፥ በውስጡም የነበሩትን ሕዝብ ተዘልለው አዩአቸው፥ አንደ ሲዶናውያንም ልማድ ጸጥ ብለው ተዘልለው ተቀምጠው ነበር፥ የሚያስቸግራቸውም የሚገዛቸውም አልነበረም፥ ከሲዶናውያንም ርቀው ከሰውም ሁሉ ተለይተው ለብቻቸው ይኖሩ ነበር። |
አባቱም በሕይወቱ ሳለ፦ “እንዲህ ለምን ታደርጋለህ?” ብሎ ከቶ ተቆጥቶት አያውቅም ነበር። ደግሞም መልከ መልካም ነበር፤ የተወለደውም ከአቤሴሎም በኋላ ነበር።
አክዓብ፥ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኃጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቁጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም።
የለመለመም እጅግም ያማረ መሰማሪያ አገኙ፥ ምድሪቱም ሰፊ ጸጥታም ያለላትና ሰላም የሰፈነባት ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ።
ገዢዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ፤ ከእርሱም ምስጋናን ታገኛለህ፤
የዳንም ልጆች ግዛታቸውን መቆጣጠር ባለልቻሉ ጊዜ ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም፤ ሌሼም የነበረውን ስምዋንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት።
ራስዋን በአከበረችበትና በተቀማጠለችበት ልክ ሥቃይንና ኀዘንን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ መበለትም አልሆንም፤ ኀዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥
ልጆቹ አስጸያፊ ነገር ሲያደርጉ እርሱ ባለመከልከሉ፥ ዔሊ በሚያውቀው ኃጢአት ምክንያት በቤተሰቡ ላይ ለዘለዓለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር።