ሑሻይም በተጨማሪ እንዲህ አለው፥ “አባትህና ሰዎቹ ብርቱ ጦረኞችና ግልገሎችዋም እንደተነጠቁባት የዱር ድብ አምርረው የሚነሡ መሆኑን ታውቃለህ፤ በተጨማሪም አባትህ በጦር ሜዳ ልምድ ያለው ነው፤ ሌሊቱን ከሠራዊቱ ጋር አያድርም፤
መሳፍንት 18:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳን ሰዎች፥ “አትሟገተን፤ ያለዚያ የተቈጡ ሰዎች ጉዳት ላይ ይጥሉሃል፤ አንተም ቤተሰብህም ሕይወታችሁን ታጣላችሁ” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳን ሰዎች፣ “አትሟገተን፤ አለዚያ የተቈጡ ሰዎች ጕዳት ላይ ይጥሉሃል፤ አንተም ቤተ ሰብህም ሕይወታችሁን ታጣላችሁ” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዳን የመጡትም ሰዎች “የተቈጡ ሰዎች አደጋ እንዳይጥሉብህና የአንተንና የቤተሰብህን ሕይወት እንዳታጣ በመካከላችን ምንም ድምፅ ባታሰማ ይሻልሃል” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳንም ልጆች እንዲህ አሉት፥ “የተቈጡ ሰዎች እንዳያገኙህና ነፍስህም፥ የቤተ ሰቦችህም ነፍስ እንዳይጠፋብህ፥ ድምፅህ በእኛ መካከል አይሰማ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳንም ልጆች፦ የተቈጡ ሰዎች እንዳይወድቁብህ ነፍስህም የቤተ ሰቦችህም ነፍስ እንዳይጠፋብህ፥ ድምፅህን በእኛ መካከል አታሰማ አሉት። |
ሑሻይም በተጨማሪ እንዲህ አለው፥ “አባትህና ሰዎቹ ብርቱ ጦረኞችና ግልገሎችዋም እንደተነጠቁባት የዱር ድብ አምርረው የሚነሡ መሆኑን ታውቃለህ፤ በተጨማሪም አባትህ በጦር ሜዳ ልምድ ያለው ነው፤ ሌሊቱን ከሠራዊቱ ጋር አያድርም፤
እርሱም፥ “እንዴት፥ ‘ምን ሆንክ’ ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ? የሠራኋቸውን አማልክቴንና ካህኔን ወስዳችሁ ሄዳችኋል፤ ምን የቀረኝ ነገር አለ?” አላቸው።
ሰዎቹ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ነፍሳቸው ተማርራ ሊወግሩት ስለ ተመካከሩ ዳዊት በጣም ተጨነቀ፤ ነገር ግን ዳዊት በአምላኩ በጌታ በረታ።