መሳፍንት 15:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወራት ሳምሶን አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ለማየት ሄደ፤ እርሱም፥ “ሚስቴ ወዳለችበት ጫጉላው ቤት ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወራት ሳምሶን አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ለማየት ሄደ፤ እርሱም፣ “ሚስቴ ወዳለችበት ጫጕላው ቤት ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወራት ሶምሶን ሚስቱን ለመጐብኘት አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሄደ፤ አባትዋንም “ሚስቴ ወዳለችበት ክፍል መግባት እፈልጋለሁ” አለው። አባትዋ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጊዜም በኋላ በስንዴ መከር ጊዜ ሶምሶን የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደና፥ “ወደ ጫጕላ ቤት ወደ ሚስቴ ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እንዳይገባ ከለከለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ በስንዴ መከር ጊዜ ሶምሶን የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደና፦ ወደ ጫጉላ ቤት ወደ ሚስቴ ልግባ አለ፥ አባትዋ ግን እንዳይገባ ከለከለው። |
“ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እርሷም መልሳ፥ “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ ምን መያዣ ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው።
በዚያን ዘመን ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ፥ እና ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፥ እነርሱም በዱሮ ዘመን፥ ስማቸው የታወቀ፥ ኃያላን ሆኑ።
እርሱ ግን መልሶ አባቱን ‘እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት አገለገልኩህ፤ ከትእዛዝህም ከቶ አልተላለፍሁም፤ ከወዳጆቼ ጋር እንድደሰት ለእኔ አንድ ጥቦት እንኳን ሰጥተኸኝ አታውቅም፤