La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 13:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ማኑሄ፥ “ጌታ ሆይ፥ የሚወለደውን ልጅ እንዴት አድርገን ማሳደግ አንዳለብን እንዲያስተምረን ያ ወደኛ የላከው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና እንዲመጣ እለምንሃለሁ” ብሎ ወደ ጌታ ጸለየ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ማኑሄ፣ “ጌታ ሆይ፤ የሚወለደውን ልጅ እንዴት አድርገን ማሳደግ አንዳለብን እንዲያስተምረን ያ ወደ እኛ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደ ገና እንዲመጣ ታደርግ ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ ማኑሄ “እግዚአብሔር ሆይ! ሕፃኑ ሲወለድ ምን ማድረግ እንደሚገባን ይነግረን ዘንድ ያ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እንደገና ተመልሶ ወደ እኛ እንዲመጣ አድርግልን” ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማኑ​ሄም፥ “ጌታ ሆይ፥ ወደ እኛ የላ​ክ​ኸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው፥ እባ​ክህ እን​ደ​ገና ወደ እኛ ይምጣ፤ ለሚ​ወ​ለ​ደ​ውም ልጅ ምን እን​ደ​ም​ና​ደ​ርግ ያስ​ገ​ን​ዝ​በን” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማኑሄም፦ ጌታ ሆይ፥ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው፥ እባክህ፥ እንደ ገና ወደ እኛ ይምጣ፥ ለሚወለደውም ልጅ ምን እንድናደርግ ያስገንዝበን ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ።

Ver Capítulo



መሳፍንት 13:8
8 Referencias Cruzadas  

የማላየውን ነገር አንተ አስተምረኝ፥ ኃጢአትንም ሠርቼ እንደሆነ፥ ደግሜ አልሠራም የሚለው ማን ነው?


እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ “ጌታ ሆይ! ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” አለው። ጌታም “ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል፤” አለው።


ማኑሄም ተነሥቶ ሚስቱን ተከተላት፤ ሰውየው እንደደረሰም፥ “ከሚስቴ ጋር ተነጋግረህ የነበርኸው አንተ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፤ “አዎን እኔ ነኝ” አለው።


የጌታም መልአክ ለሴቲቱ ተገልጦ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ አንቺ መካን ነሽ፤ ልጅም አልወለድሽም፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ።


ከዚያም ሴቲቱ ወደ ባሏ ሄዳ እንዲህ አለችው፤ “የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ የእግዚአብሔር መልአክ የሚመስልና እጅግ የሚያስደነግጥ ነበር። ከየት እንደመጣ አልጠየቅሁትም፤ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤


ነገር ግን፥ ‘ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጪ፤ ርኩስ ነገር አትብይ፤ ልጁም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ናዝራዊ በመሆን ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናልና’ ብሎኛል።”


እግዚአብሔርም የማኑሄን ጸሎት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ሴቲቱ በዕርሻ ውስጥ ሳለች ተገለጠላት፤ በዚህ ጊዜ ግን ባሏ ማኑሄ አብሮአት አልነበረም።