መሳፍንት 13:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቁርባኑ ጋር ወስዶ በዐለት ላይ ለጌታ ሠዋው። ማኑሄና ሚስቱ እያዩ ጌታ አስደናቂ ነገር አደረገ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቍርባኑ ጋራ ወስዶ በዐለት ላይ ለእግዚአብሔር ሠዋው። ማኑሄና ሚስቱ እያዩ እግዚአብሔር አስደናቂ ነገር አደረገ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ማኑሄ አንድ የፍየል ጠቦትና የእህል ቊርባን ወስዶ በአለቱ መሠዊያ ላይ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ ማኑሄና ሚስቱም እየተመለከቱ ሳለ እግዚአብሔር አስደናቂ ነገር አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው። መልአኩም ተአምራት አደረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም ይመለከቱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቁርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው። መልአኩም ተአምራት አደረገ፥ ማኑሄና ሚስቱም ይመለከቱ ነበር። |