ቁራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ፥ ስለዚህ ወደ ባርያችሁ መጥታችኋልና።” እነርሱም፦ “እንዳልህ አድርግ” አሉት።
መሳፍንት 13:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም መልአክ፥ “የግድ ብታቈየኝ እንኳ የምታቀርበውን ማንኛውንም ምግብ አልበላም፤ ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ እርሱን ለጌታ አቅርበው” አለው። የሚያነጋግረው የጌታ መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፣ “የግድ ብታቈየኝ እንኳ የምታቀርበውን ማንኛውንም ምግብ አልበላም፤ ነገር ግን የሚቃጠል መሥዋዕት የምታዘጋጅ ከሆነ እርሱን ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። የሚያነጋግረው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን “ምንም አንተ ብታቈየኝ ምግብህን አልበላም፤ የሚቃጠል መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትፈልግ ግን ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄ የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፥ “አንተ የግድ ብትለኝ እህልህን አልበላም፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ብታደርግ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም መልአክ ማኑሄን፦ አንተ የግድ ብትለኝ መብልህን አልበላም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው አለው። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አላወቀም ነበር። |
ቁራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፥ ልባችሁንም ደግፋ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ፥ ስለዚህ ወደ ባርያችሁ መጥታችኋልና።” እነርሱም፦ “እንዳልህ አድርግ” አሉት።
ሚስቱ ግን መልሳ እንዲህ አለችው፥ “ጌታ ሊገድለን ቢፈልግ ኖሮ፥ የሚቃጠለውን መሥዋትና የእህል ቁርባኑን ከእጃችን ባልተቀበለን፤ ደግሞም ይህን ነገር ሁሉ ባላሳየንና እንዲህ ያለውንም ነገር በዚህ ጊዜ ባልነገረን ነበር።”
የጌታ መልአክ፥ “ሥጋውን እርሾ ያልገባበትን ቂጣ ወስደህ፥ በዚያ ዐለት ላይ አኑር፤ መረቁንም በሥጋውና በቂጣው ላይ አፍስስ” አለው፤ ጌዴዎንም እንደ ታዘዘው አደረገ።
በዚህ ፍርስራሽ ጉብታ ላይ ለአምላክህ ለጌታ የሚገባውን መሠዊያ ሥራ። ሰባብረህ በጣልኸው የአሼራ ምስል ዐምድ ሁለተኛውን ወይፈን ወስደህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ አቅርበው።”