Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 6:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በዚህ ፍርስራሽ ጉብታ ላይ ለአምላክህ ለጌታ የሚገባውን መሠዊያ ሥራ። ሰባብረህ በጣልኸው የአሼራ ምስል ዐምድ ሁለተኛውን ወይፈን ወስደህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ አቅርበው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በዚህ ፍርስራሽ ጕብታ ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሚገባውን መሠዊያ ሥራ። ሰባብረህ በጣልኸው የአሼራ ምስል ዐምድ ሁለተኛውን ወይፈን ወስደህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ አቅርበው።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በዚያም የፍርስራሽ ጒብታ አናት ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በደንብ የተስተካከለ መሠዊያ ሥራ፤ ከዚያን በኋላ ሁለተኛውን ኰርማ ውሰድ፤ ሰባብረህ የጣልከውንም የአሼራን ምስል ስብርባሪ በማንደድ ኰርማውን በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በዚ​ያም ተራራ አናት ላይ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ አሳ​ም​ረህ ሥራ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ዉ​ንም በሬ ውሰድ፤ በዚ​ያም በቈ​ረ​ጥ​ኸው በማ​ም​ለ​ኪያ ዐጸዱ እን​ጨት ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርብ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በዚያም ኮረብታ አናት ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ አሳምረህ ሥራ ሁለተኛውንም በሬ ውሰድ፥ በዚያም በቈረጥኸው በማምለኪያ ዐፀዱ እንጨት ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርብ አለው።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 6:26
8 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ሁሉም በአግባብና በሥርዓት ይሁን።


እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ፥ የሁከት አምላክ አይደለም። በቅዱሳን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲሁ ነው።


በዚያን ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “ውጣና በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ ለጌታ መሠዊያ ሥራ” አለው።


ነገር ግን መሠዊያዎቻቸውን ታፈርሳላችሁ፥ ሐውልቶቻቸውን ትሠብራላችሁ፥ አሼራንም ትቆራርጣላችሁ፤


በዚያች ሌሊት ጌታ ጌዴዎንን እንዲህ አለው፤ “ከአባትህ መንጋ ሰባት ዓመት የሆነውን ሁለተኛውን ወይፈን ውሰድ፤ አባትህ ለበኣል የሠራውን መሠዊያ አፍርስ፤ በአጠገቡ የአሼራን ዐምድ ሰባብረህ ጣል።


ጌዴዎን ከአገልጋዮቹ ዐሥር ሰዎች ወስዶ ጌታ እንዳዘዘው አደረገ፤ ቤተሰቡንና የከተማውን ሰው ስለ ፈራ ይህን ያደረገው ቀን ሳይሆን ሌሊት ነበር።


ሠረገላውም ወደ ቤትሼሜሽ ወደ ኢያሱ እርሻ መጥቶ ቆመ። በዚያ ስፍራ አንድ ትልቅ ቋጥኝ ነበር። ሕዝቡም የሠረገላውን ዕንጨት ፈለጡት፤ ላሞቹንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ለጌታ አቀረቡ።


ኦርናም ዳዊትን እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ጌታዬ ደስ ያለውን ወስዶ መሥዋዕቱን ያቅርብ፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች፥ ለሚነደውም ዕንጨት፥ የመውቂያው ዕቃና የበሬ ቀንበር አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios