መሳፍንት 11:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአሮዔር አንሥቶ እስከ ሚኒት አካባቢ ከዚያም አልፎ እስከ ክራሚም የሚገኙትን ሃያ ከተሞች ፈጽሞ አጠፋቸው፤ አሞናውያንም ለእስራኤል ተገዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአሮዔር አንሥቶ እስከ ሚኒት አካባ፣ ከዚያም ዐልፎ እስከ ክራሚም የሚገኙትን ሃያ ከተሞች ፈጽሞ አጠፋቸው፤ አሞናውያንም ለእስራኤል ተገዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዓሮዔር ጀምሮ በሚኒት ዙሪያ እስካለው ስፍራ በአጠቃላይ ኻያ ከተሞችን፥ እንዲሁም እስከ አቤል ከራሚም ድረስ ያሉትን ሁሉ ደመሰሳቸው፤ በዚህም ዐይነት ዐሞናውያን በእስራኤላውያን ፊት ተዋረዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአሮዔርም እስከ ሚኒትና እስከ አቤልክራሚም ድረስ ሃያ ከተሞችን በታላቅ ሰልፍ አጠፋቸው። የአሞንም ልጆች በእስራኤል ልጆች ፊት ተዋረዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአሮዔርም እስከ ሚኒትና እስከ አቤልክራሚም ድረስ ሀያ ከተሞችን በታላቅ አገዳደል መታቸው። የአሞንም ልጆች በእስራኤል ልጆች ፊት ተዋረዱ። |
በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም ውስጥ ካለችው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ፥ የትኛይቱም ከተማ አልተቋቋመችንም፤ ጌታ አምላካችን ሁሉን አሳልፎ ሰጠን።