መሳፍንት 11:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሞናውያንን ድል አድርጌ በምመለስበት ጊዜ በመጀመሪያ ሊቀበለኝ ከቤቴ ደጅ የሚወጣው ማንኛውም ሰው ለጌታ ይሆናል፤ እኔም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አቀርበዋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞናውያንን ድል አድርጌ በምመለስበት ጊዜ በመጀመሪያ ሊቀበለኝ ከቤቴ ደጅ የሚወጣው ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር ይሆናል፤ እኔም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አቀርበዋለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድል አድርጌ ከዘመቻ ወደ ቤቴ በደኅና ስመለስ ከቤት ወጥቶ ሊቀበለኝ የሚመጣው ለአንተ ይሆናል፤ እርሱንም ለአንተ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አቀርበዋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአሞን ልጆች ዘንድ በደኅና በተመለስሁ ጊዜ፥ ከቤቴ ደጅ ወጥቶ የሚቀበለኝን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አደርገዋለሁ” ብሎ ለእግዚአብሔር ስእለት ተሳለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአሞን ልጆች ዘንድ በደኅና በተመለስሁ ጊዜ፥ ሊገናኘኝ ከቤቴ ደጅ የሚወጣው ማንኛውም ለእግዚአብሔር ይሆናል፥ ለሚቃጠልም መሥዋዕት አቀርበዋለሁ ብሎ ለእግዚአብሔር ስእለት ተሳለ። |
በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቁርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው። እጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል፤
ስለ ተሳልኸው ስእለት ሁሉ የአመንዝራይቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ቤት አታቅርብ፥ ሁለቱም በጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና።
እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለአገልጋይህም ወንድ ልጅ ብትሰጣት፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለጌታ እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አያርፍም።”
ሳኦል፥ “ዛሬ ጠላቶቼን ከመበቀሌ በፊት፥ እስከ ማታ ድረስ እህል የሚበላ ሰው የተረገመ ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አስምሎ ስለ ነበር፥ በዚያች ዕለት የእስራኤል ሰዎች ተጨንቀው ዋሉ፤ ስለዚህ ከሕዝቡ አንድም እህል የቀመሰ አልነበረም።