መሳፍንት 1:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያችም ምድር የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላወጡአቸውምና በመካከላቸው የአሴር ልጆች ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ምክንያት የአሴር ሕዝብ በምድሪቱ ካሉት ከነዓናውያን ጋራ ዐብረው ኖሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነዓናውያንንም ሳያስወጡ በመቅረታቸው የአሴር ሕዝብ በዚያው ከእነርሱ ጋር አብረው ይኖሩ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሴርም በዚያች ምድር በተቀመጡት ከነዓናውያን መካከል ተቀመጠ፤ ሊያጠፋቸው አልቻለምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያችም ምድር የተቀመጡትን ከነዓናውያን አላወጡአቸውምና በመካከላቸው የአሴር ልጆች ተቀመጡ። |
አሴርም በዓኮ፥ በሲዶን፥ በአሕላብ፥ በአክዚብ፥ በሒልባ፥ በኣፌቅና በረአብ የሚኖሩትን ሕዝብ በምድሪቱ ካሉት ከነዓናውያን ጋር አብረው ኖሩ።
ንፍታሌምም በቤትሳሚስና በቤትዓናት የሚኖሩትን አላስወጣም፤ ስለዚህ የንፍታሌም ነገድ በምድሪቱ ከሚኖሩት ከነዓናውያን ጋር አብረው ኖሩ፤ ይሁን እንጂ በቤትሳሚስና በቤትዓናት የሚኖሩት ለእነርሱ የጉልበት ሥራ ተገደው ይሠሩ ነበር።