መሳፍንት 1:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛብሎንም እንደዚሁ በቂድሮንና በነህሎል የነበሩትን በመካከለቸው የቀሩትን ከነዓናውያንን አላስወጣም፤ ነገር ግን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛብሎንም እንደዚሁ በቂድሮንና በነህሎል የነበሩትን በመካከላቸው የቀሩትን ከነዓናውያንን አላስወጣም፤ ነገር ግን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዛብሎን ነገድ በቂትሮንና በናህላል ይኖሩ የነበሩትን ኗሪዎች አላስወጡም ነበር፤ ስለዚህ ከነዓናውያን እዚያው ከእነርሱ ጋር ኗሪዎች ሆኑ፤ ሆኖም ለዛብሎናውያን የጒልበት ሥራ ለመሥራት ይገደዱ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛብሎንም በቄድሮንና በአማን የሚኖሩትን ሰዎች አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው ተቀመጡ፤ ግብርም የሚገብሩላቸው ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛብሎንም የቂድሮንንና የነህሎልን ሰዎች አላወጣቸውም፥ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው ተቀመጡ፥ ግብርም የሚገብሩለት ሆኑ። |
እንደዚሁም የኤፍሬም ወገኖች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያንን ማስወጣት አልቻሉም፤ ስለዚህ ከነዓናውያን በመካከላቸው እዚያው መኖርን ቀጠሉ።
አሴርም በዓኮ፥ በሲዶን፥ በአሕላብ፥ በአክዚብ፥ በሒልባ፥ በኣፌቅና በረአብ የሚኖሩትን ሕዝብ በምድሪቱ ካሉት ከነዓናውያን ጋር አብረው ኖሩ።