መሳፍንት 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካሌብም፥ “ቂርያት ሴፌርን ወግቶ ለሚይዛት ሰው ልጄን ዓክሳን እድርለታለሁ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካሌብም፣ “ቂርያትሤፍርን ወግቶ ለሚይዛት ሰው ልጄን ዓክሳንን እድርለታለሁ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካሌብም “ቀድሞ ቂርያት ሴፌርን ለሚይዝ ሰው ሴት ልጄን ዓክሳን እድርለታለሁ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካሌብም፥ “ሀገረ መጻሕፍትን ለሚመታና ለሚይዝ ልጄን ዓስካን ሚስት ትሆነው ዘንድ እሰጠዋለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካሌብም፦ ቅርያትሤፍርን ለሚመታና ለሚይዝ ልጄን ዓክሳን አጋባዋለሁ አለ። |
ተጋቡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፤ ሴቶች ልጆቻችሁንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አጋቡ፥ እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፤ በዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ።
እስራኤላውያንም እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በየቀኑ እየመጣ እስራኤልን እንደሚገዳደር ታያላችሁ? ይህን ሰው ለሚገድል፥ ንጉሡ ብዙ ሀብት ይሰጠዋል፤ ሴት ልጁን ይድርለታል፥ የአባቱንም ቤት በእስራኤል ዘንድ ከግብር ነጻ ያደርገዋል” ይባባሉ ነበር።
እነርሱም ይህንኑ ለዳዊት ደግመው ነገሩት፤ ዳዊት ግን “ለመሆኑ የንጉሥ ዐማች መሆንን እስከዚህ ትንሽ ነገር አድርጋችሁ ትቆጥራላችሁን? እኔ አንድ ምስኪን ድኻና እውቅና የሌለኝ መሆኔን አጣችሁትን?” አላቸው።