La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 5:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱ የገረዘበትም ምክንያት ይህ ነበር፤ ከግብጽ ከወጣው ሕዝብ መካከል ወንዶች ተዋጊዎች ሁሉ ከግብጽ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞተው ስለ ነበረ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንግዲህ ኢያሱ እስራኤላውያንን የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ዕድሜያቸው መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ከግብጽ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ ሳሉ በምድረ በዳ ሞቱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢያሱ እነርሱን የገረዘበት ምክንያት ከግብጽ ምድር የወጡት ለወታደርነት ብቃት የነበራቸው ወንዶች ሁሉ በበረሓው ጒዞ ጊዜ ሞተው ስለ ነበረ ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያሱ ሕዝ​ቡን ሁሉ የገ​ረ​ዘ​በት ምክ​ን​ያት ይህ ነው፤ ከግ​ብፅ የወጡ ወን​ዶች ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ በመ​ን​ገድ ላይ በም​ድረ በዳ ሞቱ፤ የወ​ጡ​ትም ወን​ዶች ሁሉ ተገ​ር​ዘው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱ የገረዘበትም ምክንያት ይህ ነው፥ ከግብፅ የወጡት ሕዝብ ወንዶች ሰልፈኞች ሁሉ ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ በምድረ በዳ ሞቱ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 5:4
8 Referencias Cruzadas  

በግብጽ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ክብሬንና ተአምራቴን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ እኔን ስለ ተፈታተኑኝ፥ ድምፄንም ስላልሰሙ፥


እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ በአብዛኞቹ ደስ አልተሰኘም፤ እነርሱ ምድረ በዳ ወድቀው ቀርተዋልና።


የዘሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ ጌታ እንደ ማለባቸው የጦረኞች ትውልድ ሁሉ ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።


“እንዲህም ሆነ፥ ጦረኞቹ ከጠፉ ከሕዝቡም መካከል ከሞቱ በኋላ፥


ኢያሱም የባልጩት መቁረጫ ሠርቶ የግርዛት ኮረብታ በተባለ ስፍራ የእስራኤልን ልጆች ገረዘ።


የወጡት ሕዝብ ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ነገር ግን ከግብጽ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ በመንገድ እየተጓዙ ሳሉ የተወለዱት ልጆች ሁሉ አልተገረዙም ነበር።