ኢያሱ 24:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበሰበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምንቶቻቸውንም ጠራ። እነርሱም በጌታ ፊት ቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢያሱ የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ በሴኬም ሰበሰበ፤ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች፣ መሪዎች፣ ፈራጆችና ሹማምት ጠራ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱ የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ በሴኬም በአንድነት ሰበሰበ፤ ሽማግሌዎችን፥ አለቆቻቸውን፥ ዳኞችንና የእስራኤልን የጦር አዛዦች ሁሉ ጠራ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ተሰበሰቡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴሎ ሰበሰበ፤ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች፥ አለቆቻቸውንም፥ ጸሓፊዎቻቸውንም፥ ፈራጆቻቸውንም ጠራቸው። በእግዚአብሔርም ፊት አቆማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበሰበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምቶቻቸውንም ጠራ። እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ። |
እነርሱም በእጃቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ፥ እንዲሁም በጆሮአቸውም ያሉትን ጉትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፥ ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የባሉጥ ዛፍ በታች ቀበራቸው።
ስለዚህ ያንጊዜ ወደ አንተ ላክሁ፤ አንተም በመምጣትህ መልካም አድርገሃል። እንግዲህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዝኸውን ሁሉ እንድንሰማ እኛ ሁላችን አሁን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን።”
በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት-አርባቅን ለዩ።
ኢያሱ እስራኤልን ሁሉ ሽማግሌዎቻቸውንም አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምንቶቻቸውንም ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ ሸምግያለሁ፥ ዕድሜዬም ገፍቷል፤
የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ ወደ ቤቴል ወጡ፤ እዚያም እያለቀሱ በጌታ ፊት ተቀመጡ፤ በዚያን ቀን እስኪመሽ ድረስ ጾሙ፤ በጌታ ፊት የሚቃጠል መሥዋትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ።
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ንቃችሁ፤ ‘የለም፤ ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ። ስለዚህ በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ሆናችሁ በጌታ ፊት ቅረቡ።”