La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 20:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳያስበው በድንገት ሰው የገደለ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ወደ ተለዩት ከተሞች መሸሽ ይችላል፤ በማኅበሩ ፊት ከመቆሙ አስቀድሞም በደም ተበቃዩ መገደል የለበትም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለእስራኤል ሕዝብና በመካከላቸውም ለሚኖሩ መጻተኞች መማጸኛ ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ማንም ሰው በድንገተኛ አጋጣሚ ሰው ቢገድል፥ በሸንጎ ሳይፈረድበት እንዳይገደል ከእነዚያ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሄዶ ሊበቀለው ከሚፈልገው ሰው እጅ ያመልጣል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በማ​ኅ​በሩ ፊት እስ​ኪ​ቆ​ምና እስ​ኪ​መ​ረ​መር ድረስ ባለ​ደሙ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው ሳያ​ውቅ ሰውን የገ​ደለ ወደ​ዚያ እን​ዲ​ማ​ፀን፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ በመ​ካ​ካ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ቀ​መጥ መጻ​ተኛ የተ​መ​ረጡ ከተ​ሞች እነ​ዚህ ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው።

Ver Capítulo



ኢያሱ 20:9
5 Referencias Cruzadas  

የምትሰጡአቸውም ስድስቱ ከተሞች የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ።


በስሕተት ነፍስ የገደለ ሁሉ እንዲሸሽበት እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸው ለሚቀመጡ እንግዶችና መጻተኞች መማፀኛ ይሆናሉ።


ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ በከተማይቱ ሽማግሌዎች ጆሮ ነገሩን ይናገራል፤ እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚቀመጥበትም ስፍራ ይሰጡታል ከእነርሱም ጋር ይቀመጣል።


በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያም ወራት ያለው ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ፤ ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ይመለሳል፥ ወደ ከተማውም ወደ ቤቱም ሸሽቶ ወደ ወጣበትም ከተማ ይገባል።’ ”


በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ።