ኢያሱ 20:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ በከተማይቱ ሽማግሌዎች ጆሮ ነገሩን ይናገራል፤ እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚቀመጥበትም ስፍራ ይሰጡታል ከእነርሱም ጋር ይቀመጣል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ገዳዩ ከነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በሚሸሽበት ጊዜ፣ በከተማዪቱ መግቢያ በር ላይ ቆሞ ጕዳዩን ለከተማዪቱ ሽማግሌዎች ይንገራቸው፤ ከዚያም እነርሱ ወደ ከተማቸው አስገብተው የሚኖርበትን ስፍራ ሰጥተውት ዐብሯቸው ይቀመጥ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እርሱም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ፈጥኖ በመሄድ በከተማይቱ መግቢያ በር ወደሚገኘው ፍርድ ሸንጎ ቀርቦ የሆነውን ነገር ሁሉ ለመሪዎቹ ይገልጣል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ከተማይቱ እንዲገባ ይፈቅዱለታል፤ የሚኖርበትንም ስፍራ ይሰጡትና በዚያ ይቈያል፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ከእነዚህም ከተሞች በአንዲቱ ይማፀናል፤ በከተማዪቱም በር አደባባይ ቆሞ ለከተማዪቱ ሽማግሌዎች ነገሩን ይናገራል፤ እነርሱም ወደ ከተማዪቱ ያገቡታል። የሚቀመጥበትም ስፍራ ይሰጡታል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ በከተማይቱ ሽማግሌዎች ጆሮ ነገሩን ይናገራል፥ እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚቀመጥበትም ስፍራ ይሰጡታል። Ver Capítulo |