La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 20:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነዚህም ከተሞች በስሕተት ሳያውቅም ሰውን የገደለ ገዳይ እንዲሸሽባቸው ከደም ተበቃዩ መማፀኛ ይሆኑላችኋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳያስበው ድንገት ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው ወደዚያ በመሸሽ ከደም ተበቃዩ እንዲያመልጥ ከተማዪቱ መጠለያ ትሁን።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ማንም ሰው ሳያውቅ በድንገት ሰው ቢገድል፥ ወደዚያ በመሄድ ሊበቀለው ከሚፈልገው ሰው ይድናል፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ባለ​ማ​ወቅ ሳይ​ወ​ድድ ሰውን የገ​ደለ በዚያ ይማ​ፀን ዘንድ፥ ለእ​ና​ንተ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞ​ችን ሥሩ፤ ነፍስ የገ​ደለ ሰውም በአ​ደ​ባ​ባይ ለፍ​ርድ እስ​ኪ​ቀ​ርብ ድረስ በደም ተበ​ቃዩ አይ​ገ​ደል።

Ver Capítulo



ኢያሱ 20:3
8 Referencias Cruzadas  

እርሷም፥ “ደም ተበቃዮቹ ተጨማሪ ደም እንዳያፈሱ ልጄም እንዳይገደል፥ ንጉሡ ጌታ አምላኩን ያስብ” አለች። ንጉሡም፥ “ሕያው በሆነው ጌታ እምላለሁ! ከልጅሽ አንድ ጠጉር በምድር ላይ አይወድቅም” አላት።


“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ማናቸውም ሰው ባለማወቅ ጌታ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ተላልፎ ኃጢአት ቢሠራ፥


ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹ ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ።


ደም ተበቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳዩን ይግደል፤ ባገኛው ጊዜ ይግደለው።


“ነገር ግን ያለ ጥላቻ ድንገት ገፍትሮ ቢጥለው፥ ሳይሸምቅም አንዳች ነገር ቢጥልበት፥


ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።


“ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘በሙሴ አማካይነት የነገርኋችሁን መማፀኛ ከተሞችን ለዩ፤


ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ በከተማይቱ ሽማግሌዎች ጆሮ ነገሩን ይናገራል፤ እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚቀመጥበትም ስፍራ ይሰጡታል ከእነርሱም ጋር ይቀመጣል።