La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 19:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ተምናሴራ የምትባለውን ከተማ እንደ ጌታ ትእዛዝ ሰጡት፤ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት በኰረብታማው የኤፍሬም ምድር የምትገኘውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ ሰጡት፤ እርሱም ከተማዪቱን ሠራ፤ መኖሪያውም አደረጋት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት በኮረብታማው በኤፍሬም አገር እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ቲምናትሴራሕ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ሰጡት፤ ያቺንም ከተማ እንደገና ሠርቶ መኖሪያው አደረጋት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ራማ ሀገር ያለ​ች​ውን ተም​ና​ሴራ የም​ት​ባ​ለ​ውን የፈ​ለ​ጋ​ትን ከተማ ሰጡት፤ ከተ​ማም ሠርቶ ተቀ​መ​ጠ​ባት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጡት፥ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት።

Ver Capítulo



ኢያሱ 19:50
6 Referencias Cruzadas  

የእነዚህም ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸውም ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፥ ቤንሑር፦ ኰረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤


ሴት ልጁም ታችኛውንና ላይኛውን ቤት-ሖሮንንና ኡዜን-ሼራን የሠራች ሲኦራ ነበረች።


ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ ሆሴአ፤


ምድሩንም ሁሉ በየግዛቱ ርስት እንዲሆን አከፋፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት።


በተራራማው በኤፍሬም አገር በገዓስ ተራራ በሰሜን ባለችው በርስቱ ግዛት በተምና-ሴራ ቀበሩት።


እነርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በምትገኘው ከገዓስ ተራራ በስተ ሰሜን ባለችው በራሱ ርስት ላይ በቲምናሔሬስ ቀበሩት።