ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቁጥራቸው ኻያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጽር ተንዶባቸው አለቁ። ቤንሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ በመግባት ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ።
ኢያሱ 19:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዑማ፥ አፌቅ፥ ረዓብ ደግሞ ነበሩ፤ ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የዑማን፣ የአፌቅንና የረአብን ምድር ይጨምራል። በዚህም ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ይገኛሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዑማ፥ አፌቅና ረሖብ ተብለው የሚጠሩትን ኻያ ሁለት ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙ ታናናሽ ከተሞችን ይጨምራል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርኮብ፥ አፌቅ፥ ረአውም ደግሞ ነበሩ፤ ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዑማ፥ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ፥ ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ከሞት የተረፉትም ሶርያውያን ሸሽተው ወደ አፌቅ ከተማ ገቡ፤ በዚያም ቁጥራቸው ኻያ ሰባት ሺህ በሚሆኑት ወታደሮች ላይ የከተማው ቅጽር ተንዶባቸው አለቁ። ቤንሀዳድም አምልጦ ወደ ከተማይቱ በመግባት ከአንድ ቤት በስተ ኋላ በኩል ባለው ክፍል ውስጥ ተደበቀ።
አሴርም በዓኮ፥ በሲዶን፥ በአሕላብ፥ በአክዚብ፥ በሒልባ፥ በኣፌቅና በረአብ የሚኖሩትን ሕዝብ በምድሪቱ ካሉት ከነዓናውያን ጋር አብረው ኖሩ።
የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤል ሁሉ ደረሰ። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ሊወጉ ወጡ፤ እነርሱ በአቤንኤዘር ሲሰፍሩ፥ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ በአፌቅ ሰፈሩ።