ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው በዓል ሄዱ።
ኢያሱ 15:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ከዚያም ተነስቶ ወደ ዔፍሮን ተራራ ከተሞች ወጣ፤ ቂርያት-ይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ታጠፈ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በመቀጠል ከተራራው ዐናት ተነሥቶ ወደ ኔፍቶ ምንጮች በማምራት፣ በዔፍሮን ተራራ ላይ ያሉትን ከተሞች ዐልፎ ይወጣና ቂርያትይዓይሪም ተብሎ ወደሚጠራው ወደ በኣላ ቍልቍል ይወርዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ድንበሩ ከተራራው ጫፍ ተነሥቶ ወደ ኔፍቶሐ ምንጮች ይደርሳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ይወጣል፤ ወደ ባዓላ ወይም ቂርያት ይዓሪም ይታጠፋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄዳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ይደርሳል፤ ወደ ኢያሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ደረሰ፥ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ወጣ፥ ቂርያትይዓሪም ወደምትባል ወደ በኣላ ደረሰ። |
ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው በዓል ሄዱ።
ዳዊትም እስራኤልም ሁሉ በኪሩቤል ላይ የተቀመጠውን ስሙም በእርሱ የተጠራውን የጌታን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው ቂርያት-ይዓሪም ወደተባለች ወደ በኣላ ሄዱ።
ወጥተውም በይሁዳ ምድር ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፤ እንግዲህ ከቂርያትይዓሪም በስተ ምዕራብ ያለው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር መባሉ ከዚህ የተነሣ ነው።
ከዚያም ወደ ቂርያትይዓሪም ሰዎች መልእክተኞች ልከው፥ “ፍልስጥኤማውያን የጌታን ታቦት መልሰውልናል፤ መጥታችሁ ወደ እናንተ ውሰዱት” አሏቸው።