ዮናስ 4:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ዮናስን ከቶ ደስ አላሰኘውም፥ ክፉኛም አበሳጨው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናስ ግን ፈጽሞ አልተደሰተም፤ ስለዚህም ተቈጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናስ በዚህ ነገር ስላልተደሰተ ተበሳጨ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናስም ፈጽሞ አዘነ፤ ተከዘም። |
የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፦ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፤ ኀጢአተኛ ናትና፤” ሲል በልቡ አሰበ።
ጳውሎስና በርናባስም ገልጠው “የእግዚአብሔር ቃል አስቀድሞ ለእናንተ ይነገር ዘንድ ያስፈልጋል፤ ከገፋችሁትና የዘለዓለም ሕይወት እንዳይገባችሁ በራሳችሁ ከፈረዳችሁ ግን፥ እነሆ፥ ወደ አሕዛብ ዘወር እንላለን።