ዮናስ 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፦ ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ አልሁ ነገር ግን ቅዱስ መቅደስህን ዳግም አያለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውሃ እስከ ዐንገቴ አጠለቀኝ፤ ጥልቁም ከበበኝ፤ የባሕርም ዐረም በራሴ ላይ ተጠመጠመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውሃ እስከ አንገቴ ድረስ አጠለቀኝ፤ ባሕርም ፈጽሞ አሰጠመኝ፤ በባሕር ውስጥም የበቀለው ሣር ቅጠል በራሴ ላይ ተጠመጠመብኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም፦ ከዐይንህ ፊት ተጣልሁ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁን? አልሁ። |