ዮናስ 1:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አሉት፦ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን ምን እናድርግብህ?” ባሕሩ መናወጡን ቀጥሎ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባሕሩም ማዕበል እጅግ እየበረታ ስለ ሄደ፣ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባሕሩም ማዕበል እየበረታ በመሄዱ መርከበኞቹ “ይህ ማዕበል ጸጥ እንዲል በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” ሲሉ ጠየቁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሕሩ ይታወክ ነበርና፥ ታላቅ ማዕበልም ተነሥቶ ነበርና፥ “ባሕሩ ጸጥ ይልልን ዘንድ እንግዲህ ምን እናድርግህ?” አሉት። |