ዮሐንስ 8:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ “አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም “ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርሁት ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “ለመሆኑ፣ አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እስካሁን የነገርኋችሁ እኔ እርሱ ነኝ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ከመጀመሪያ አንሥቼ እንደ ነገርኳችሁ ነኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “አንተ ማነህ?” አሉት፤ ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “በመጀመሪያ ነግሬአችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ፦ “አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም፦ “ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርሁት ነኝ። |
ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ፤” አላቸው።