ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትን ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝቡ መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዘዋወር ነበር።
ዮሐንስ 6:59 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቅፍርናሆም፥ በምኵራብ ሲያስተምር ነበር ይህን ያለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን የተናገረው በቅፍርናሆም፣ በምኵራብ እያስተማረ ሳለ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ይህን የተናገረው በቅፍርናሆም በምኲራብ በሚያስተምርበት ጊዜ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቅፍርናሆምም በምኵራብ ሲያስተምራቸው ይህን ተናገረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቅፍርናሆም ሲያስተምር ይህን በምኵራብ አለ። |
ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትን ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝቡ መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዘዋወር ነበር።
ኢየሱስም መልሶ “እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም ምንም አልተናገርሁም።