ዮሐንስ 5:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ አታድንቁ፤ በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚህ አትደነቁ፤ መቃብር ውስጥ ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ነገር አትደነቁ፤ በመቃብር ውስጥ ያሉት ሁሉ የእርሱን ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በመቃብር ያሉ ሁሉ ቃሉን የሚሰሙባት ጊዜ ትመጣለችና ስለዚህ አታድንቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ መልካምም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ። |
ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ፥ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤ ሞት ሆይ! ቸነፈርህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! አጥፊነትህ ወዴት አለ? ርኅራኄ ከዓይኔ ተሰወረች።
ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል፤ ይኸውም አሁን ነው፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።
ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ! በዚህ ስለምን ትደነቃላችሁ? ወይስ በገዛ ኀይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድ እንዳደረግነው ስለምን ትኩር ብላችሁ ታዩናላችሁ?
ሙታንን፥ እንዲሁም ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት በተጻፈው መሠረት፥ እንደ ሥራቸው መጠን ፍርድን ተቀበሉ።