ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
ዮሐንስ 3:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምስክርነቱን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደሆነ አረጋገጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምስክርነቱንም የተቀበለ ሰው፣ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አረጋገጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእርሱን ምስክርነት የሚቀበል ግን እግዚአብሔር እውነተኛ መሆኑን ያረጋግጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምስክርነቱን የተቀበለ ግን እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ። |
ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”
ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ፤” አላቸው።
ሳይገረዝም በእምነቱ ባገኘው የጽድቅ ማኅተም፥ መገረዝን እንደ ምልክት ተቀበለ፤ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ፥ ለእነርሱም ጽድቅ ሆኖ እንዲቆጠርላቸው አባት ነውና፤
እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል ሰምታችሁ፥ በክርስቶስም አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤
ሆኖም የእግዚአብሔር ጠንካራ መሠረት የቆመው፦ “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለውን ማኅተም ታትሞ ነው።