ዮሐንስ 19:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መቃብሩም ቅርብ ስለ ነበረና የአይሁድ የዝግጅት ቀን ስለ ነበረ ኢየሱስን በዚያ አኖሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕለቱ ለአይሁድ የሰንበት መዘጋጃ ቀን ስለ ነበርና መቃብሩም ቅርብ ስለ ነበር ኢየሱስን በዚያ ቀበሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰንበት ዝግጅት ቀን ስለ ነበረና መቃብሩም ቅርብ ስለ ነበረ የኢየሱስን አስከሬን እዚያ ቀበሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስንም በዚያ ቀበሩት፤ ለአይሁድ የመሰናዳት ቀን ነበርና፤ መቃብሩም ለሰቀሉበት ቦታ ቅርብ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ አኖሩት። |
ዮናስ በዓሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁም የሰው ልጅ በምድር ልብ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይቆያል።
ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር።
አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥ እንዲሁም ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና፥ ሥጋቸው በሰንበት ቀን በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት።