ዮሐንስ 19:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ ቀደም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ አንድ መቶ ሊትር ያህል የሚመዝን የከርቤና የአደስ ቅልቅል ይዞ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በፊት በሌሊት ወደ ኢየሱስ ሄዶ የነበረው ኒቆዲሞስም አንድ መቶ ነጥርየሚያኽል የከርቤና የሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረው ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀብሩበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። |
ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቶ በተሞላው አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የመቃብር ወግ አደረጉለት።
ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅ፥ ዕጣንና ከርቤ አቀረቡለት።
ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቶ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጉርዋም አበሰቻችው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።