ዮሐንስ 19:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ የሆነው “ከእርሱ አጥንት አይሰበርም” የሚለው የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሆነው፣ መጽሐፍ፣ “ከዐጥንቱ አንድም አይሰበርም” ያለው እንዲፈጸም፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሆነው፥ “ከእርሱ አንድ አጥንት እንኳ አይሰበርም” የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ሁሉ የሆነው “ከእርሱ ዐፅሙን አትስበሩ” ያለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ የሆነ፦ “ከእርሱ አጥንት አይሰበርም” የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። |
ስለ ሁላችሁም አይደለም የምናገረው፤ እኔ የመረጥኋቸውን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ቅዱስ መጽሐፍ ‘እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣብኝ’ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።
ስለዚህም እርስ በርሳቸው “ለማን እንዲሆን ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው” ተባባሉ። ይህም “ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነበር። ወታደሮቹም እንዲህ አደረጉ።